እነዚያም የማግቢያን ጣጣ የማያገኙ አላህ ከችሮታው እስከሚያከብራቸው ድረስ ይጠበቁ፡፡ እነዚያንም እጆቻችሁ ከጨበጧቸው አገልጋዮች (ገንዘብ ሰጥተው ነጻ ለመውጣት) መጻጻፍን የሚፈልጉትን ከእነሱ መልካምን ነገር ብታውቁ ተጻጻፉዋቸው፡፡ ከአላህም ገንዘብ ከዚያ ከሰጣችሁ ስጧቸው፡፡ ሴቶች ባሮቻችሁንም መጥጠበቅን ቢፈልጉ የቅርቢቱን ሕይወት ጥቅም ለመፈለግ ብላችሁ በዝሙት ላይ አታስገድዱዋቸው፡፡ የሚያስገድዳቸውም ሰው አላህ ከመገደዳቸው በኋላ (ለተገደዱት) መሓሪ አዛኝ ነው፡፡
An-Nur 24:33
Compare 2 Amharic translations
وَلْيَسْتَعْفِفِ الَّذِينَ لَا يَجِدُونَ نِكَاحًا حَتَّىٰ يُغْنِيَهُمُ اللَّهُ مِنْ فَضْلِهِ ۗ وَالَّذِينَ يَبْتَغُونَ الْكِتَابَ مِمَّا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ فَكَاتِبُوهُمْ إِنْ عَلِمْتُمْ فِيهِمْ خَيْرًا ۖ وَآتُوهُمْ مِنْ مَالِ اللَّهِ الَّذِي آتَاكُمْ ۚ وَلَا تُكْرِهُوا فَتَيَاتِكُمْ عَلَى الْبِغَاءِ إِنْ أَرَدْنَ تَحَصُّنًا لِتَبْتَغُوا عَرَضَ الْحَيَاةِ الدُّنْيَا ۚ وَمَنْ يُكْرِهْهُنَّ فَإِنَّ اللَّهَ مِنْ بَعْدِ إِكْرَاهِهِنَّ غَفُورٌ رَحِيمٌ
DragHold to move · × to hide
እነዚያም የማግቢያን ጣጣ የማያገኙ ሰዎች አላህ ከችሮታው እስከሚያከብራቸው ድረስ ራሳቸውን (ከዝሙት) ይጠብቁ። እነዚያንም እጆቻችሁ ከጨበጧቸው አገልጋዮች መካከል ገንዘብ ሰጥተው ነጻ ለመውጣት መጻጻፍን የሚፈልጉትን ከእነርሱ መልካም ነገርን ብታውቁ (ብታዩ) ተጻጻፏቸው። አላህ ከሰጣችሁ ገንዘብም ስጧቸው። ሴቶች ባሮቻችሁንም መጠበቅን ከፈለጉ የቅርቢቱን ህይወት ጥቅም ለመፈለግ ብላችሁ በዝሙት ተግባር ላይ አታስገድዷቸው። የሚያስገድዳቸዉም ሰው አላህ ከመገደዳቸው በኋላ ለተገደዱት መሓሪና አዛኝ ነውና።