An-Nur 24:58

Compare 2 Amharic translations

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لِيَسْتَأْذِنْكُمُ الَّذِينَ مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ وَالَّذِينَ لَمْ يَبْلُغُوا الْحُلُمَ مِنْكُمْ ثَلَاثَ مَرَّاتٍ ۚ مِنْ قَبْلِ صَلَاةِ الْفَجْرِ وَحِينَ تَضَعُونَ ثِيَابَكُمْ مِنَ الظَّهِيرَةِ وَمِنْ بَعْدِ صَلَاةِ الْعِشَاءِ ۚ ثَلَاثُ عَوْرَاتٍ لَكُمْ ۚ لَيْسَ عَلَيْكُمْ وَلَا عَلَيْهِمْ جُنَاحٌ بَعْدَهُنَّ ۚ طَوَّافُونَ عَلَيْكُمْ بَعْضُكُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ ۚ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمُ الْآيَاتِ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እነዚያ እጆቻችሁ የጨበጧቸው (ባሮች) እነዚያም ከእናንተ ለአካላ መጠን ያልደረሱት ከጎህ ስግደት በፊት፣ በቀትርም ልብሶቻችሁን በምታወልቁ ጊዜ ከምሽት ስግደትም በኋላ ሦስት ጊዜያት (ለመግባት ሲፈልጉ) ያስፈቅዷችሁ፡፡ (እነዚህ) ለእናንተ የኾኑ ሦስት የሐፍረተ ገላ መገለጫ ጊዜያቶች ናቸውና፡፡ ከእነዚህ በኋላ በእናንተም በእነርሱም ላይ (ያለፈቃድ በመግባት) ኀጢአት የለም፡፡ በእናንተ ላይ (ለማገልገል) ዙዋሪዎች ናቸውና፡፡ ከፊላችሁ በከፊሉ ላይ ዙዋሪ ነው፡፡ እንደዚሁ አላህ ለእናንተ ሕግጋትን ይገልጽላችኋል፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እነዚያ እጆቻችሁ የጨበጧቸው ባሮች እነዚያም ከናንተ መካከል ለአካለ መጠን ያልደረሱት (ህፃናት) በሶስት ጊዜ: ከጎህ ስግደት በፊት፤ በቀትር ልብሶቻችሁን በምታወልቁበት ጊዜና ከምሽት ስግደትም በኋላ ወደ እናንተ ለመግባት ሲፈልጉ ያስፈቅዷችሁ። እነዚህ የእናንተ ሶስት የሐፍረተ ገላ መግለጫ ጊዜያቶች ናቸውና። ከእነዚህ በኋላ ግን በእናንተም ሆነ በነሱ ላይ (ያለፈቃድ በመግባት) ኃጢአት የለም። እናንተን ለማገልገል በዙሪያችሁ ዟሪዎች ናቸውና። ከፊላችሁ በከፊሉ ላይ ዟሪ ነውና፤ ልክ እንደዚሁ አላህ ለእናንተ ህግጋቱን ይገልጽላችኋል። አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና።

Africa Academy