Fussilat 41:44

Compare 2 Amharic translations

وَلَوْ جَعَلْنَاهُ قُرْآنًا أَعْجَمِيًّا لَقَالُوا لَوْلَا فُصِّلَتْ آيَاتُهُ ۖ أَأَعْجَمِيٌّ وَعَرَبِيٌّ ۗ قُلْ هُوَ لِلَّذِينَ آمَنُوا هُدًى وَشِفَاءٌ ۖ وَالَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ فِي آذَانِهِمْ وَقْرٌ وَهُوَ عَلَيْهِمْ عَمًى ۚ أُولَٰئِكَ يُنَادَوْنَ مِنْ مَكَانٍ بَعِيدٍ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

በአጀምኛ የኾነ ቁርኣን ባደረግነው ኖሮ አንቀጾቹ «(በምናውቀው ቋንቋ) አይብራሩም ኖሯልን? (ቁርኣኑ) አጀምኛና (መልክተኛው) ዐረባዊ ይኾናልን?» ባሉ ነበር እርሱ ለእነዚያ ለአመኑት መምሪያና መፈወሻ ነው፡፡ እነዚያም የማያምኑት በጆሮዎቻቸው ውስጥ ድንቁርና ነው፡፡ (አይሰሙትም)፡፡ እርሱ በእነርሱ ላይ እውርነት ነው፡፡ እነዚያ ከሩቅ ስፍራ እንደሚጥጠሩ ናቸው፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአዕጀምኛ የሆነ ቁርኣን ባደረግነው ኖሮ «አናቅጹ በምናውቀው ቋንቋ አይብራሩም ኖሯልን? (ቁርኣኑ) አዕጀምኛና (መልዕክተኛው) አረባዊ ይሆናልን?» ባሉ ነበር። እርሱ ለእነዚያ በአላህ ላመኑት ሰዎች መመሪያና መፈወሻ ነው በላቸው። እነዚያም የማያምኑት በጆሮዎቻቸው ውስጥ ድንቁርና ነው (አይሰሙትም)። እርሱ በእነርሱ ላይ እውርነት ነው። እነዚያ ከሩቅ ስፍራ እንደሚጠሩ ናቸው።

Africa Academy