Muhammad 47:4

Compare 2 Amharic translations

فَإِذَا لَقِيتُمُ الَّذِينَ كَفَرُوا فَضَرْبَ الرِّقَابِ حَتَّىٰ إِذَا أَثْخَنْتُمُوهُمْ فَشُدُّوا الْوَثَاقَ فَإِمَّا مَنًّا بَعْدُ وَإِمَّا فِدَاءً حَتَّىٰ تَضَعَ الْحَرْبُ أَوْزَارَهَا ۚ ذَٰلِكَ وَلَوْ يَشَاءُ اللَّهُ لَانْتَصَرَ مِنْهُمْ وَلَٰكِنْ لِيَبْلُوَ بَعْضَكُمْ بِبَعْضٍ ۗ وَالَّذِينَ قُتِلُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ فَلَنْ يُضِلَّ أَعْمَالَهُمْ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

እነዚያንም የካዱትን (በጦር ላይ) ባገኛችሁ ጊዜ ጫንቃዎችን በኀይል ምቱ፡፡ ባደካማችኋቸውም ጊዜ (አትግደሏቸው ማርኳቸው)፡፡ ማሰሪያውንም አጥብቁ፡፡ በኋላም ወይም በነጻ ትለቋቸዋላችሁ፤ ወይም ትበዧቸዋላችሁ፡፡ (ይህም) ጦሪቱ መሳሪያዋን እስከምትጥል ድረስ ነው፡፡ (ነገሩ) ይህ ነው፡፡ አላህም ቢሻ ከእነርሱ (ያለጦር) በተበቀለ ነበር፡፡ ግን ከፊላችሁን በከፊሉ ሊሞክር (በዚህ አዘዛችሁ)፡፡ እነዚያንም በአላህ መንገድ ላይ የተገደሉትን ሥራዎቻቸውን ፈጽሞ አያጠፋባቸውም፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

አማኞች ሆይ! እነዚያንም የካዱትን ሰዎች በጦር ላይ ባገኛችኋቸው ጊዜ ጫንቃዎችን በሀይል ምቱ። ባደከማችኋቸው ጊዜም አትግደሏቸው፤ ማርኳቸው። ማሰሪያውንም አጥብቁ። በኋላም በነጻ ትለቋቸዋላችሁ። ወይም ፊዳ ታስከፍሏቸዋላችሁ። ይህም ጦሩ መሳሪያዉን እስከሚጥል ድረስ ነው። ነገሩ ይህ ነው። አላህም ቢፈልግ ከእነርሱ ያለ ጦር በተበቀለ ነበር ግን ከፊላችሁን በከፊሉ ሊሞክር (በዚህ አዘዛችሁ)። እነዚያንም በአላህ መንገድ ላይ የተገደሉት ሰዎች ስራዎቻቸውን ፈጽሞ አያጠፋባቸዉም።

Africa Academy