Al-An'am 6:144

Compare 2 Amharic translations

وَمِنَ الْإِبِلِ اثْنَيْنِ وَمِنَ الْبَقَرِ اثْنَيْنِ ۗ قُلْ آلذَّكَرَيْنِ حَرَّمَ أَمِ الْأُنْثَيَيْنِ أَمَّا اشْتَمَلَتْ عَلَيْهِ أَرْحَامُ الْأُنْثَيَيْنِ ۖ أَمْ كُنْتُمْ شُهَدَاءَ إِذْ وَصَّاكُمُ اللَّهُ بِهَٰذَا ۚ فَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّنِ افْتَرَىٰ عَلَى اللَّهِ كَذِبًا لِيُضِلَّ النَّاسَ بِغَيْرِ عِلْمٍ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الظَّالِمِينَ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

ከግመልም ሁለትን ከከብትም ሁለትን (ፈጠረ)፡፡«አላህ (ከሁለቱ) ወንዶቹን እርም አደረገን ወይስ ሴቶቹን ወይስ የሁለቱ ሴቶች ማሕፀኖች በእርሱ ላይ ያጠቃለሉትን? በእውነቱ አላህ በዚህ ባዘዛችሁ ጊዜ የተጣዳችሁ ነበራችሁን? ሰዎችንም ያለ ዕውቀት ሊያጠም በአላህ ላይ ውሸትን ከቀጠፈ ሰው ይበልጥ በደለኛ ማን ነው? (የለም) አላህ በደለኞችን ሕዝቦች (ቅኑን መንገድ) አይመራም፡፡»

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

ከግመል ሁለትን፤ ከከብት ሁለትን ፈጠረ። «አላህ ከሁለቱ ወንዶችን ብቻ እርም አደረገን? ወይንስ ሴቶችን ብቻ? ወይስ የሁለቱ ሴቶች ማህጸኖች ያጠቃለሉትን? በእውነቱ አላህ በዚህ ነገር ባዘዛችሁ ጊዜ በቦታው ነበራችሁን? ሰዎችን ያለ እውቀት ሊያጠም በአላህ ላይ ውሸትን ከቀጠፈ ሰው ይበልጥ በደለኛ ማን ነው? አላህ በደለኞችን ህዝቦች ቅኑን መንገድ አይመራም።» በላቸው።

Africa Academy