Al-An'am 6:145

Compare 2 Amharic translations

قُلْ لَا أَجِدُ فِي مَا أُوحِيَ إِلَيَّ مُحَرَّمًا عَلَىٰ طَاعِمٍ يَطْعَمُهُ إِلَّا أَنْ يَكُونَ مَيْتَةً أَوْ دَمًا مَسْفُوحًا أَوْ لَحْمَ خِنْزِيرٍ فَإِنَّهُ رِجْسٌ أَوْ فِسْقًا أُهِلَّ لِغَيْرِ اللَّهِ بِهِ ۚ فَمَنِ اضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَإِنَّ رَبَّكَ غَفُورٌ رَحِيمٌ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

(ሙሐመድ ሆይ!) በላቸው፡- «ወደእኔ በተወረደው ውስጥ በክት ወይም ፈሳሽ ደም ወይም የአሳማ ስጋ እርሱ ርኩስ ነውና ወይም በአመጽ ከአላህ ስም ሌላ በእርሱ ላይ የተወሳበት ካልኾነ በስተቀር በሚመገበው ተመጋቢ ላይ እርም የኾነን ነገር አላገኝም፡፡ አመጸኛና ወሰን ያለፈ ሳይኾንም የተገደደ ሰው (ከተወሱት ቢበላ ኃጢአት የለበትም)፡፡ ጌታህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡»

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ወደ እኔ በተወረደው ቁርኣን ውስጥ በክት ወይም የፈሰሰ ደም፤ ወይም የአሳማ ስጋ እርሱ እርኩስ ነውና፤ ወይም በአመጽ ከአላህ ስም ሌላ በእርሱ ላይ የተወሳበት ካልሆነ በስተቀር ተመጋቢ ላይ እርም የሆነ ነገር አላገኝም። አመጸኛና ወሰን ያለፈ ሳይሆን የተገደደ ሰው (ከተወሱት ነገሮች ነፍስን የማዳን ያህል ቢበላ ኃጢአት የለበትም)። ጌታህ መሀሪና አዛኝ ነውና።» በላቸው።

Africa Academy