«የየቲምንም ገንዘብ ብርታቱን (አካለ መጠን) እስኪ ደርስ ድረስ በዚያች እርሷ መልካም በኾነች ኹኔታ እንጅ አትቅረቡ፡፡ ስፍርንና ሚዛንንም በትክክሉ ሙሉ፡፡ ነፍስን ችሎታዋን እንጂ አናስገድድም፡፡ በተናገራችሁም ጊዜ በዘመዶቻችሁ ላይ ቢኾንም እንኳ (እውነትን በመናገር) አስተካክሉ፡፡ በአላህም ቃል ኪዳን ሙሉ፡፡ እነሆ ትገሰጹ ዘንድ በርሱ አዘዛችሁ፡፡»
Al-An'am 6:152
Compare 2 Amharic translations
وَلَا تَقْرَبُوا مَالَ الْيَتِيمِ إِلَّا بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ حَتَّىٰ يَبْلُغَ أَشُدَّهُ ۖ وَأَوْفُوا الْكَيْلَ وَالْمِيزَانَ بِالْقِسْطِ ۖ لَا نُكَلِّفُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا ۖ وَإِذَا قُلْتُمْ فَاعْدِلُوا وَلَوْ كَانَ ذَا قُرْبَىٰ ۖ وَبِعَهْدِ اللَّهِ أَوْفُوا ۚ ذَٰلِكُمْ وَصَّاكُمْ بِهِ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ
DragHold to move · × to hide
«የየቲምንም ገንዘብ አካለ መጠን እስኪደርስ ድረስ በመልካም ሁኔታ እንጂ አትቅረቡ። ስፍርንና ሚዛንንም በትክክል ሙሉ። ማንኛዋም ነፍስ የችሎታዋን ያህል እንጂ አናስገድድም። በተናገራችሁ ጊዜ በዘመዶቻችሁ ላይ ቢሆንም እንኳ እውነትን በመናገር አስተካክሉ። በአላህ ቃል ኪዳን ሙሉ። ይሀችሁ ትገሰጹ ዘንድ አላህ በእርሱ አዘዛችሁ።