እርሱም ያ ከሰማይ ውሃን ያወረደ ነው፡፡ በርሱም የነገሩን ሁሉ በቃይ አወጣን፡፡ የተደራረበንም ቅንጣት ከርሱ የምናወጣ የኾነን ለምለም (አዝመራ) ከርሱ አወጣን፡፡ ከዘንባባም ከእንቡጧ የተቀራረቡ የኾኑ ዘለላዎች አሉ፡፡ ከወይኖችም፣ ከወይራም፣ ከሩማንም (ቅጠላቸው) ተመሳሳይና (ፍሬያቸው) የማይመሳሰል ሲኾኑ አትክልቶችን (አወጣን)፡፡ ባፈራ ጊዜ ወደ ፍሬውና ወደ መብሰሉ ተመልከቱ፡፡ በእነዚህ ተዓምራት ለሚያምኑ ሕዝቦች ምልክቶች አሉ፡፡
Al-An'am 6:99
Compare 2 Amharic translations
وَهُوَ الَّذِي أَنْزَلَ مِنَ السَّمَاءِ مَاءً فَأَخْرَجْنَا بِهِ نَبَاتَ كُلِّ شَيْءٍ فَأَخْرَجْنَا مِنْهُ خَضِرًا نُخْرِجُ مِنْهُ حَبًّا مُتَرَاكِبًا وَمِنَ النَّخْلِ مِنْ طَلْعِهَا قِنْوَانٌ دَانِيَةٌ وَجَنَّاتٍ مِنْ أَعْنَابٍ وَالزَّيْتُونَ وَالرُّمَّانَ مُشْتَبِهًا وَغَيْرَ مُتَشَابِهٍ ۗ انْظُرُوا إِلَىٰ ثَمَرِهِ إِذَا أَثْمَرَ وَيَنْعِهِ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكُمْ لَآيَاتٍ لِقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ
DragHold to move · × to hide
እርሱ (አላህ) ያ ከሰማይ ውሃን ያወረደ አምላክ ነው። በእርሱም የሁሉንም ዓይነት እጽዋት አበቀልን። የተደራረበን ቅንጣት የምናወጣበትን ለምለም አዝመራም ከርሱ አወጣን። ከዘንባባ እንቡጥም የተቀራረቡ የሆኑ ዘለላዎችን አወጣን። የወይን አትክልት ቦታዎችን አዘጋጀን። ቅጠሎቻቸው የሚመሳሰሉ ፍሬዎቻቸው ግን የማይመሳሰሉ የሆኑትን የዘይቱን(ወይራ) እና የሩማን እጽዋትም ከሰማይ ባወረድነው ዝናብ አበቀልን። (የሰው ልጆች ሆይ!) ፍሬውን ባፈራና በበሰለ ጊዜ እስቲ ተመልከቱት (እጅግ አስደናቂ ሆኖ ታገኙታላችሁ)። በእነዚህ ክስተቶች ውስጥ በትክክል በአላህ ለሚያምኑ ሰዎች ሁሉ በርካታ ተአምራት አሉበት።