Al-Mumtahina 60:1

Compare 2 Amharic translations

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا عَدُوِّي وَعَدُوَّكُمْ أَوْلِيَاءَ تُلْقُونَ إِلَيْهِمْ بِالْمَوَدَّةِ وَقَدْ كَفَرُوا بِمَا جَاءَكُمْ مِنَ الْحَقِّ يُخْرِجُونَ الرَّسُولَ وَإِيَّاكُمْ ۙ أَنْ تُؤْمِنُوا بِاللَّهِ رَبِّكُمْ إِنْ كُنْتُمْ خَرَجْتُمْ جِهَادًا فِي سَبِيلِي وَابْتِغَاءَ مَرْضَاتِي ۚ تُسِرُّونَ إِلَيْهِمْ بِالْمَوَدَّةِ وَأَنَا أَعْلَمُ بِمَا أَخْفَيْتُمْ وَمَا أَعْلَنْتُمْ ۚ وَمَنْ يَفْعَلْهُ مِنْكُمْ فَقَدْ ضَلَّ سَوَاءَ السَّبِيلِ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ጠላቶቼንና ጠላቶቻችሁን ወዳጆች አድርገችሁ አትያዙ፡፡ ከእውነቱ የመጣላችሁን ሃይማኖት በእርግጥ የካዱ ሲኾኑ ውዴታን ወደእነርሱ ታደርሳላችሁ፡፡ መልክተኛውንና እናንተን በአላህ በጌታችሁ ስላመናችሁ (ከመካ) ያወጣሉ፡፡ በመንገዴ ለመታገልና ውዴታዬን ለመፈለግ የወጣችሁ እንደኾናችሁ (ወዳጆች አድርጋችሁ አትያዙዋቸው)፡፡ እኔ የምትደብቁትንና የምትገልጹትን ሁሉ የማውቅ ስኾን ወደእነርሱ በፍቅር ትመሳጠራላችሁ፡፡ ከእናንተም (ይህንን) የሚሠራ ሰው ቀጥተኛውን መንገድ በእርግጥ ተሳሳተ፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ጠላቶቼንና ጠላቶቻችሁን ወዳጆች አድርጋችሁ አትያዙ። የመጣላችሁን ትክክለኛ ሃይማኖት የካዱ ሲሆኑ ውዴታን ለእነርሱ ታደርጋላችሁ። እነርሱ መልዕክተኛውንና እናንተን በጌታችሁ በአላህ ስላመናችሁ ብቻ ከሀገራችሁ አስወጧችሁ። በመንገዴ ለመታገልና ውዴታየን ለመፈለግ የወጣችሁ እንደሆናችሁ እነርሱን ወዳጆች አድርጋችሁ አትያዟቸው። እኔ የምትደብቁትንና የምትገልጹትን የማውቅ ስሆን ከእነርሱ ጋር ፍቅር ትመሳጠራላችሁ። ከናንተ መካከልም ይህንን የሚፈጽም ሰው ቀጥተኛውን መንገድ በእርግጥ ስቷል።

Africa Academy