እላንተ ያመናችሁ ሆይ! ምእምናት ስደተኞች ኾነው በመጧችሁ ጊዜ (ለሃይማኖት መሰደዳቸውን) ፈትኑዋቸው፡፡ አላህ በእምነታቸው ይበልጥ ዐዋቂ ነው፡፡ አማኞችም መኾናቸውን ብትውቁ ወደ ከሓዲዎቹ አትመልሱዋቸው፡፡ እነርሱ (ሴቶቹ) ለእነርሱ የተፈቀዱ አይደሉምና፡፡ እነርሱም (ወንዶቹ) ለእነርሱ አይፈቀዱምና፡፡ ያወጡትንም ገንዘብ ስጧቸው፡፡ መህራቸውንም በሰጣችኋቸው ጊዜ ብታገቡዋቸው በእናንተ ላይ ኃጢአት የለባችሁም፡፡ የከሓዲዎቹንም ሴቶች የጋብቻ ቃል ኪዳኖች አትያዙ፤ ያወጣችሁትንም ገንዘብ ጠይቁ፡፡ ያወጡትንም ይጠይቁ፡፡ ይህ የአላህ ፍርድ ነው፡፡ በመካከላችሁ ይፈርዳል፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡
Al-Mumtahina 60:10
Compare 2 Amharic translations
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا جَاءَكُمُ الْمُؤْمِنَاتُ مُهَاجِرَاتٍ فَامْتَحِنُوهُنَّ ۖ اللَّهُ أَعْلَمُ بِإِيمَانِهِنَّ ۖ فَإِنْ عَلِمْتُمُوهُنَّ مُؤْمِنَاتٍ فَلَا تَرْجِعُوهُنَّ إِلَى الْكُفَّارِ ۖ لَا هُنَّ حِلٌّ لَهُمْ وَلَا هُمْ يَحِلُّونَ لَهُنَّ ۖ وَآتُوهُمْ مَا أَنْفَقُوا ۚ وَلَا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ أَنْ تَنْكِحُوهُنَّ إِذَا آتَيْتُمُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ ۚ وَلَا تُمْسِكُوا بِعِصَمِ الْكَوَافِرِ وَاسْأَلُوا مَا أَنْفَقْتُمْ وَلْيَسْأَلُوا مَا أَنْفَقُوا ۚ ذَٰلِكُمْ حُكْمُ اللَّهِ ۖ يَحْكُمُ بَيْنَكُمْ ۚ وَاللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ
DragHold to move · × to hide
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሴት ምዕመናት ስደተኞች ሆነው ወደ እናንተ በሚመጡበት ጊዜ (ለሀይማኖት ሲሉ መሰደዳቸውን) ፈትኗቸው። አላህ በእምነታቸው ከናንተ ይልቅ አዋቂ ነው። ትክክለኛ አማኞችም መሆናቸውን ብታውቁ ወደ ከሓዲያን ባሎቻቸው አትመልሷቸው። እነርሱ ሙስሊም ሴቶች ለከሓዲ ወንዶች አይፈቀዱምና። ከሓዲያን ወንዶችም ለአማኝ ሴቶች የተፈቀዱ አይደሉምና። ያወጡትንም ገንዘብ መህሩን ስጧቸው። መህራቸውንም ከሰጣችኋቸው ብታገቧቸው ኃጢአት የለባችሁም ። የከሓዲያት ሚስቶቻችሁንም የጋብቻ ቃል ኪዳኖች አትያዙ። ሆኖም እናንተ ያወጣችሁትን ገንዘብ ጠይቁ ። እነርሱም ያወጡትን ይጠይቁ። ይህ የአላህ ፍርድ ነውና። በመካከላችሁም ይፈርዳል። አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው።