Al-Mumtahina 60:4

Compare 2 Amharic translations

قَدْ كَانَتْ لَكُمْ أُسْوَةٌ حَسَنَةٌ فِي إِبْرَاهِيمَ وَالَّذِينَ مَعَهُ إِذْ قَالُوا لِقَوْمِهِمْ إِنَّا بُرَآءُ مِنْكُمْ وَمِمَّا تَعْبُدُونَ مِنْ دُونِ اللَّهِ كَفَرْنَا بِكُمْ وَبَدَا بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمُ الْعَدَاوَةُ وَالْبَغْضَاءُ أَبَدًا حَتَّىٰ تُؤْمِنُوا بِاللَّهِ وَحْدَهُ إِلَّا قَوْلَ إِبْرَاهِيمَ لِأَبِيهِ لَأَسْتَغْفِرَنَّ لَكَ وَمَا أَمْلِكُ لَكَ مِنَ اللَّهِ مِنْ شَيْءٍ ۖ رَبَّنَا عَلَيْكَ تَوَكَّلْنَا وَإِلَيْكَ أَنَبْنَا وَإِلَيْكَ الْمَصِيرُ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

በኢብራሂምና በእነዚያ ከእርሱ ጋር በነበሩት (ምእምናን) መልካም መከተል አለቻችሁ፡፡ ለሕዝቦቻቸው «እኛ ከእናንተ ከአላህ ሌላ ከምትግገዙትም ንጹሖች ነን፡፡ በእናንተ ካድን፡፡ በአላህ አንድ ብቻ ሲኾን እስከምታምኑ ድረስ በእኛና በእናንተ መካከል ጠብና ጥላቻ ዘወትር ተገለጸ፡፡» ባሉ ጊዜ (መልካም መከተል አለቻችሁ)፡፡ ኢብራሂም ለአባቱ «እኔ ለአንተ ከአላህ (ቅጣት) ምንም የማልጠቅም ስኾን ለአንተ በእርግጥ ምሕረትን እለምንልኻለሁ» ማለቱ ብቻ ሲቀር፡፡ «ጌታችን ሆይ! በአንተ ላይ ተመካን፡፡ ወደ አንተም ተመለስን መመለሻም ወደ አንተ ብቻ ነው፤» (ባለው ተከተሉት)፡፡......

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

ኢብራሂምና እነዚያ ከእርሱ ጋር አብረው የነበሩት አማኞች ለእናንተ መልካም አርአያ ናቸው። ይኸዉም ለህዝቦቻቸው «እኛ ከናንተና ከዚያ ከአላህ ሌላ ከምትገዙት ጣዖታት ሁሉ ንጹሆች ነን። በእናንተም ካድን። በአላህ አንድነት እስከምታምኑ ድረስ በእኛና በእናንተ መካከል ጠብና ጥላቻ ዘወትር ተገለጸ።» ባሉ ጊዜ ኢብራሂም ለአባቱ፡- «ላንተ ከአላህ ቅጣት ምንም የማልጠቅምህ (የማላድንህ) ስሆን ላንተ በእርግጥ ምህረትን እለምንልሃለሁ።» ማለቱ ብቻ ሲቀር «ጌታችን ሆይ ባንተ ላይ ተመካን ወደ አንተም ተመለስን መመለሻም ወደ አንተ ብቻ ነው።» (ባለው ተከተሉ።)

Africa Academy