ከሰዓቲቱ መቼ እንደምትረጋ (እንደምትመጣ) ይጠይቁሃል፡፡ «ዕውቀቷ በጌታዬ ዘንድ ነው፡፡ በጊዜዋ እርሱ እንጂ ሌላ አይገልጣትም፡፡ በሰማያትና በምድርም ከበደች፡፡ በድንገት ቢኾን እንጂ አትመጣችሁም» በላቸው፡፡ ከእርሷ አጥብቀህ እንደ ተረዳህ አድርገው ይጠይቁሃል፡፡ «ዕውቀቷ አላህ ዘንድ ብቻ ነው፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም» በላቸው፡፡
Al-A'raf 7:187
Compare 2 Amharic translations
يَسْأَلُونَكَ عَنِ السَّاعَةِ أَيَّانَ مُرْسَاهَا ۖ قُلْ إِنَّمَا عِلْمُهَا عِنْدَ رَبِّي ۖ لَا يُجَلِّيهَا لِوَقْتِهَا إِلَّا هُوَ ۚ ثَقُلَتْ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ لَا تَأْتِيكُمْ إِلَّا بَغْتَةً ۗ يَسْأَلُونَكَ كَأَنَّكَ حَفِيٌّ عَنْهَا ۖ قُلْ إِنَّمَا عِلْمُهَا عِنْدَ اللَّهِ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ
DragHold to move · × to hide
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ትንሳኤ መቼ እንደምትመጣ ይጠይቁሃል። «እውቀቷ በጌታዬ ዘንድ ብቻ ነው። በመከሰቻዋ ጊዜም እርሱ እንጂ ሌላ አይገልጽላችሁም። በሰማያትና በምድርም ከበደች። በድንገት ቢሆን እንጂ አትመጣባችሁም።» በላቸው። ስለ እርሷ በደንብ እንደተረዳህ አድርገው ይጠይቁሃል። «እውቀቷ ግን አላህ ዘንድ ብቻ ነው። ግን አብዛኞቹ ሰዎች ይህን ነገር ጠንቅቀው አያውቁም።» በላቸው።