ከጦር ዘረፋ ገንዘቦች ይጠይቁሃል፡፡ «የዘረፋ ገንዘቦች የአላህና የመልክተኛው ናቸው፡፡» ስለዚህ አላህን ፍሩ፡፡ በመካከላችሁ ያለችውንም ኹኔታ አሳምሩ፡፡ አማኞችም እንደኾናችሁ አላህንና መልክተኛውን ታዘዙ በላቸው፡፡
Al-Anfal 8:1
Compare 2 Amharic translations
يَسْأَلُونَكَ عَنِ الْأَنْفَالِ ۖ قُلِ الْأَنْفَالُ لِلَّهِ وَالرَّسُولِ ۖ فَاتَّقُوا اللَّهَ وَأَصْلِحُوا ذَاتَ بَيْنِكُمْ ۖ وَأَطِيعُوا اللَّهَ وَرَسُولَهُ إِنْ كُنْتُمْ مُؤْمِنِينَ
DragHold to move · × to hide
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በጦርነት ከተማረኩ ገንዘቦች ይጠይቁሃል። «በጦርነት የተማረኩ ገንዘቦች የአላህና የመልዕክተኛው ናቸው። ስለዚህ አላህን ፍሩ። በመካከላችሁ ያለውንም ሁኔታ አሳምሩ። ትክክለኛ አማኞች ከሆናችሁ አላህንና መልዕክተኛውን ታዘዙ።» በላቸው።