The Backbiter · al-Humazah · سورة الهمزة · 9 ayahs

القرآن الكريمAfrica Academy

بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።

وَيْلٌ لِكُلِّ هُمَزَةٍ لُمَزَةٍ

ለሐሜተኛ፤ ለዘላፊ፤ (ለአሽሟጣጭ ሁሉ) ወዮለት።

الَّذِي جَمَعَ مَالًا وَعَدَّدَهُ

ለዚያ ገንዘብን የሰበሰበና የቆጣጠረው (ያደለበዉም) ለሆነ ሁሉ ወዮለት።

يَحْسَبُ أَنَّ مَالَهُ أَخْلَدَهُ

ገንዘቡ በዚህች ዓለም ዘውታሪ እንደሚያደርገው ያስባል።

كَلَّا ۖ لَيُنْبَذَنَّ فِي الْحُطَمَةِ

በጭራሽ፤ አውዳሚና የምትፈጭ በሆነችው እሳት ውስጥ በእርግጥ ይጣላል።

وَمَا أَدْرَاكَ مَا الْحُطَمَةُ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የምትፈጨዋም ምን እንደሆነች ምን አሳወቀህ?

نَارُ اللَّهِ الْمُوقَدَةُ

የተቀጣጠለችው የአላህ እሳት ናት።

الَّتِي تَطَّلِعُ عَلَى الْأَفْئِدَةِ

ያቺ በልቦች ላይ እንኳን ሳይቀር የምትዘልቅ የሆነች።

إِنَّهَا عَلَيْهِمْ مُؤْصَدَةٌ

እርሷ በእርግጥ በእነርሱ ላይ የተዘጋች ናት።

فِي عَمَدٍ مُمَدَّدَةٍ

በተዘረጋች አዕማድ ውስጥ የተዘጋች ናት።