Al-Baqarah 2:85

Compare 2 Amharic translations

ثُمَّ أَنْتُمْ هَٰؤُلَاءِ تَقْتُلُونَ أَنْفُسَكُمْ وَتُخْرِجُونَ فَرِيقًا مِنْكُمْ مِنْ دِيَارِهِمْ تَظَاهَرُونَ عَلَيْهِمْ بِالْإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ وَإِنْ يَأْتُوكُمْ أُسَارَىٰ تُفَادُوهُمْ وَهُوَ مُحَرَّمٌ عَلَيْكُمْ إِخْرَاجُهُمْ ۚ أَفَتُؤْمِنُونَ بِبَعْضِ الْكِتَابِ وَتَكْفُرُونَ بِبَعْضٍ ۚ فَمَا جَزَاءُ مَنْ يَفْعَلُ ذَٰلِكَ مِنْكُمْ إِلَّا خِزْيٌ فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا ۖ وَيَوْمَ الْقِيَامَةِ يُرَدُّونَ إِلَىٰ أَشَدِّ الْعَذَابِ ۗ وَمَا اللَّهُ بِغَافِلٍ عَمَّا تَعْمَلُونَ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

ከዚያም እናንተ እነዚያ ነፍሶቻችሁን የምትገድሉ ከናንተም የኾኑ ጭፍሮችን በኃጢአትና በመበደል በነርሱ ላይ የምትረዳዱ ስትኾኑ ከአገሮቻቸው የምታወጡ ምርኮኞችም ኾነው ቢመጡዋችሁ የምትበዡ ናችሁ፡፡ እርሱ (ነገሩ) እነርሱን ማውጣት በእናንተ ላይ የተከለከለ ነው፡፡ በመጽሐፉ ከፊል ታምናላችሁን? በከፊሉም ትክዳላችሁን? ከእናንተም ይህንን የሚሠራ ሰው ቅጣት በቅርቢቱ ሕይወት ውርደት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ በትንሣኤ ቀንም ወደ ብርቱ ቅጣት ይመለሳሉ፡፡ አላህም ከምትሠሩት ሥራ ሁሉ ዘንጊ አይደለም፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

ከዚያም ቃል ኪዳናችሁን በማፍረስ ወገኖቻችሁን የምትገድሉ፤ ከናንተም መካከል የሆኑ ሕዝቦችን በኃጢአትና በመበደል ላይ በመተባበር ከአገሮቻቸው የምታስወጡ እናንተው ራሳችሁ ናችሁ። ምርኮኞች ሆነው ወደ እናንተ ሲመጡም ቤዛ ትሆኗቸዋላችሁ። እነርሱን ከመኖሪያ ክልላቸው ማባረሩ በእናንተ ላይ የተከለከለ ነው። በመጽሐፉ በከፊሉ አምናችሁ በሌላው ትክዳላችሁን? ከእናንተ መካከል ይህንን ጸያፍ ተግባር የሚሰራ ሰው ሁሉ ቅጣቱ በቅርቢቱ ሕይወት ውርደት እንጂ ሌላ አይደለም። በትንሳኤ ቀንም ወደ ብርቱ ቅጣት ይመለሳሉ። አላህ ከምትሰሩት ዘንጊ አይደለም።

Africa Academy