Al-Mujadilah 58:4

Compare 2 Amharic translations

فَمَنْ لَمْ يَجِدْ فَصِيَامُ شَهْرَيْنِ مُتَتَابِعَيْنِ مِنْ قَبْلِ أَنْ يَتَمَاسَّا ۖ فَمَنْ لَمْ يَسْتَطِعْ فَإِطْعَامُ سِتِّينَ مِسْكِينًا ۚ ذَٰلِكَ لِتُؤْمِنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ ۚ وَتِلْكَ حُدُودُ اللَّهِ ۗ وَلِلْكَافِرِينَ عَذَابٌ أَلِيمٌ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

ያላገኘም ሰው ከመነካከታቸው በፊት ሁለት የተከታተሉ ወሮችን መጾም አለበት፡፡ ያልቻለም ሰው ስድሳ ድኾችን ማብላት (አለበት)፡፡ ይህ በአላህና በመልክተኛው እንድታምኑ ነው፡፡ ይህችም የአላህ ሕግጋት ናት፡፡ ለከሓዲዎችም አሳማሚ ቅጣት አልላቸው፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

ይህን ላላገኘም ሰው ከመነካካታቸው በፊት ሁለት ተከታታይ ወሮችን መፆም አለበት። ይህን ላልቻለም ሰው ስልሳ ድሆችን ማብላት አለበት። ይህ በአላህና በመልዕክተኛው እንድታምኑ ነው። እነኚህ ህግጋት የአላህ ህግጋት ናቸው። (እናም አትተላለፏቸው።) ለከሓዲያንም ሁሉ አሳማሚ ቅጣት አለባቸው።

Africa Academy